Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 24:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጪ ባለ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፥ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበት ጊዜ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እዚያም እንደ ደረሰ፣ ግመሎቹን ከከተማው ውጭ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ አንበረከከ፤ ጊዜውም ውሃ ለመቅዳት የሚወጣበት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሲመሽም ሴቶች ውኃ ሊቀዱ በሚወጡበት ጊዜ ከከተማይቱ ውጪ በውኃው ጉድጓድ አጠገብ ግመሎቹን አስበረከከ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሲመ​ሽም ውኃ ቀጂ​ዎች ውኃ ሊቀዱ በሚ​መ​ጡ​በት ጊዜ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ውጪ በውኃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ግመ​ሎ​ቹን አሳ​ረፈ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሲመሽም ሴቶች ውኃ ሊቀዱ በሚወጡበት ጊዜ ከከተማይቱ ውጪ በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ግመሎቹን አሰበ ረከከ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 24:11
10 Referencias Cruzadas  

“ከዚህም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጒድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፥


እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጒድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጒድጓዱ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጒድጓድ ነበር፤ ጒድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤


ንጉሡም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ሙሴን ለማስገደል ፈለገ፤ ሙሴ ግን ኰብልሎ በዚያው ለመኖር ወደ ምድያም አገር ሄደ። እዚያም እንደ ደረሰ በውሃ ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤


አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ።


ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


በዚያን ጊዜ አንዲት የሰማርያ አገር ሴት ውሃ ልትቀዳ ወደ ጒድጓዱ መጣች፤ ኢየሱስም “ውሃ አጠጪኝ!” አላት።


እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።


በዳገቱ አድርገው ወደ ከተማው ሲወጡ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው “ባለ ራእይ እዚህ አለን?” ብለው ጠየቁአቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos