1 ሳሙኤል 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሞት የተረፉትም የእባጩ በሽታ በርትቶባቸው ስለ ነበር ሕዝቡ ርዳታ ለማግኘት ወደ አማልክታቸው በማልቀስ ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያልሞቱትን ደግሞ ዕባጩ ያሠቃያቸው ስለ ነበር፣ የከተማዪቱ ጩኸት እስከ ሰማይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያልሞቱትን ደግሞ ዕባጩ ያሠቃያቸው ስለ ነበር፥ የከተማዪቱ ጩኸት እስከ ሰማይ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ታቦት ወደዚያ በገባች ጊዜ በከተማው ሁሉ ታላቅ ሁከት ሆኖአልና። በሕይወትም ያሉ፥ ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፤ የከተማዪቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፥ የከተማይቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ። |
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡና መኳንንቱ፥ መላውም የግብጽ ሕዝብ ሁሉ ከእንቅልፋቸው ነቁ፤ ወንድ ልጅ ያልሞተበት አንድ ቤት እንኳ ስላልነበረ በግብጽ ምድር ሁሉ ታላቅ የለቅሶ ጩኸት አስተጋባ።
“ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።
“እናንተ መሪዎች አልቅሱ፤ እናንተ የሕዝብ ጠባቂዎች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ዋይ፥ ዋይ!’ በሉ፤ በዐመድ ላይ እየተንከባለላችሁ እዘኑ፤ ሁላችሁም የምትታረዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ውድ የሆነ የሸክላ ዕቃ ሲወድቅ ተሰብሮ እንደሚበታተን፥ እናንተም ትበታተናላችሁ።
ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል።
“ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ጩኸታቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ ወደ ሕዝቤ ተመልክቼአለሁና ከፍልስጥኤማውያን ጭቈና ሕዝቤን ስለሚያድን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው።”