1 ሳሙኤል 4:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ በማዋለድ የምትረዳት ሴት “አይዞሽ በርቺ! ወንድ ልጅ ወልደሻል!” አለቻት፤ ነገር ግን አዳምጣ መልስ አልሰጠቻትም፤ አላተኰረችበትምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፣ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፣ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፥ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፥ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሞትም በቀረበች ጊዜ በዙሪያዋ ያሉት ሴቶች “ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ” አሉአት። እርስዋ ግን አልመለሰችላቸውም፤ ልብዋም አያስታውስም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሞትም በቀረበች ጊዜ በዙሪያዋ ያሉት ሴቶች፦ ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ አሉአት። እርስዋ ግን አልመለሰችላቸውም፥ በልብዋም አላኖረችውም። |
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
ሴት በምትወልድበት ጊዜ የምጥ ቀንዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ከወለደች በኋላ ግን በዓለም ላይ ሕፃን ስለ ተወለደ ከመደሰትዋ የተነሣ ጭንቀትዋን አታስታውሰውም።
የፊንሐስ ሚስት የነበረችው የዔሊ ምራት ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት መማረኩን፤ ዐማትዋና ባልዋ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ በድንገተኛ ምጥ ተይዛ ወለደች፤ ምጡም ጸንቶባት ነበር፤