1 ሳሙኤል 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ተማረከ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ታቦት ተማረከች፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ታቦት ተማረከች፥ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ። |
እኔ እንድመለክበት በመጀመሪያ መርጬው ወደነበረው ቦታ ወደ ሴሎ ሂዱ፤ እዚያም ምን እንዳደረግሁት ተመልከቱ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ኃጢአት ምክንያት ሴሎን ደመሰስኩት።
እነሆ፥ ከአንተ ቤተሰብ መካከል አንድም ሰው ወደ ሽምግልና ዕድሜ እንዳይደርስ አንተንና የአባቶችህን ቤተሰብ የማጠፋበት ጊዜ እየተቃረበ ነው።
እነሆ እኔ በምመለክበት ቦታ ብዙ ችግር ታያለህ፤ በእስራኤል ዘንድ በጎ ነገር የሚደረግ ቢሆንም ከአንተ ቤተሰብ መካከል ማንም ረጅም ዕድሜ የሚኖረው አይገኝም።
በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤