እግዚአብሔር ይህን ያዘዛችሁ ከዚያ ዛፍ ፍሬ በበላችሁ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑና ደጉን ከክፉ ለይታችሁ እንደምታውቁ ስለሚያውቅ ነው”፤
1 ሳሙኤል 28:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዐይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ቅጣት አያገኝሽም” ሲል በእግዚአብሔር ስም ማለላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዓይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው ጌታ ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” ሲል በጌታ ስም ማለላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ክፉ አያገኝሽም ብሎ በእግዚአብሔር ማለላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ቅጣት አያገኝሽም ብሎ በእግዚአብሔር ማለላት። |
እግዚአብሔር ይህን ያዘዛችሁ ከዚያ ዛፍ ፍሬ በበላችሁ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑና ደጉን ከክፉ ለይታችሁ እንደምታውቁ ስለሚያውቅ ነው”፤
እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! የልጄን ሞት ለመበቀል ኀላፊነት የተቀበለው ዘመዴ ሌላውን ልጄን በመግደል የባሰ ወንጀል እንዳይፈጽም ታደርገው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ” አለችው። ንጉሥ ዳዊትም “በልጅሽ ላይ ጒዳት መድረስ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ እንኳ አንዲቱ መሬት ላይ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሻለሁ” አላት።
በደል ሠርቶ የተገኘው ሰው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን በሞት እንደሚቀጣ ለእስራኤል ድልን በሰጠው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።” ነገር ግን አንዳች መልስ የሰጠው ሰው አልተገኘም።
ሴትዮዋም “ንጉሥ ሳኦል ያደረገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህ፤ እርሱ እኮ ጠንቋዮችንና ሙታን ጠሪዎችን ከእስራኤል ምድር አጥፍቶአቸዋል፤ ታዲያ አንተ እኔን አጥምደህ ልታስገድለኝ የምትፈልገው ስለምንድን ነው?” ስትል መለሰችለት።