ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።
1 ሳሙኤል 28:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት የጦር ሠራዊታቸውን ሰበሰቡ፤ አኪሽም ዳዊትን “አንተና ተከታዮችህ ከእኔ ጐን ተሰልፋችሁ መዋጋት እንደሚገባችሁ በእርግጥ ዕወቅ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዘመን ፍልስጥኤማውያን፣ እስራኤልን ለመውጋት ሰራዊታቸውን ሰበሰቡ። አንኩስም ዳዊትን፣ “አንተና ሰዎችህ ዐብራችሁኝ ለጦርነት መውጣት እንዳለባችሁ ዕወቁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ዘመን ፍልስጥኤማውያን፥ እስራኤልን ለመውጋት ሠራዊታቸውን ሰበሰቡ። አኪሽም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ አብራችሁኝ ለጦርነት መውጣት እንዳለባችሁ ትረዳኛለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእስራኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ጭፍሮቻቸውን ለሰልፍ ሰበሰቡ፤ አንኩስም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እንድትወጡ በርግጥ ዕወቅ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በዚያ ወራት ከእስራኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ጭፍሮቻቸውን ለሰልፍ ሰበሰቡ፥ አንኩስም ዳዊትን፦ አንተና ሰዎችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እንድትወጡ በእርግጥ እወቅ አለው። |
ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።
ፍልስጥኤማውያን ሶኮ ተብላ በምትጠራው በይሁዳ ለጦርነት ተሰለፉ፤ እነርሱም በሶኮና በዐዜቃ መካከል ኤፌስዳሚም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፍረው ነበር።
አኪሽ ግን ዳዊትን ስለሚተማመንበት በልቡ “በወገኖቹ በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ የተጠላ ስለ ሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያገለግለኛል” በማለት ያስብ ነበር።
እስራኤላውያን በምጽጳ መሰብሰባቸውንም ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች አደጋ ሊጥሉባቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈሩ።