1 ሳሙኤል 26:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት ጦሩንና ውሃ መቅጃውን ከሳኦል ራስጌ አንሥቶ እርሱና አቢሳ ከዚያ ሄዱ፤ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከባድ እንቅልፍ ልኮባቸው ተጫጭኖአቸው ተኝተው ስለ ነበር ይህ ሁሉ ሲሆን ማንም ነቅቶ ያየና ያወቀ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ አጠገብ የነበረውን ጦርና የውሃውን መያዣ ወሰደ፤ ከዚያም ሄዱ፤ ይህን ያየም ሆነ ያወቀ ወይም የነቃ ማንም አልነበረም። ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ስለ ወደቀባቸው ሁሉም ተኝተው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ አጠገብ የነበረውን ጦርና የውሃውን መያዣ ወሰደ፤ ከዚያም ሄዱ፤ ይህን ያየም ሆነ ያወቀ ወይም የነቃ ማንም አልነበረም። ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ስለ ወደቀባቸው ሁሉም ተኝተው ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፤ ወደ ቤታቸውም ተመለሱ። ማንም ያየ አልነበረም፤ ያወቃቸውም ማንም አልነበረም፤ የነቃም ማንም አልነበረም፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሳኦል ራስ አጠገብ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፥ ማንም ሳያይ ሳያውቅም ሄዱ፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር እንጂ የነቃ አልነበረም። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐኑ አጥንቶች አንዱን ወሰደና ባዶውን ቦታ በሥጋ ሞላው፤
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ።
ተከታዮቹም ዳዊትን “እነሆ፥ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልሃል! እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ እንደሚጥልልህ ነግሮሃል፤ እነሆ፥ አሁን በጠላትህ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ!” አሉት፤ ዳዊትም በልቡ እየተሳበ በመቅረብ ሳኦል ሳያውቅ ከልብሱ ጫፍ ላይ ቈርጦ ወሰደ፤
ስለዚህም በዚያው ምሽት ዳዊትና አቢሳን ወደ ሳኦል ሰፈር ገቡ፤ ሳኦልንም በሰፈሩ መካከል ተኝቶ አገኙት፤ ጦሩም በራስጌው በኩል መሬት ላይ ተተክሎ ነበር፤ አበኔርና ወታደሮቹም በዙሪያው ተኝተዋል፤