Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐኑ አጥንቶች አንዱን ወሰደና ባዶውን ቦታ በሥጋ ሞላው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጌታ እግዚአብሔርም አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በአ​ዳም ላይ እን​ቅ​ል​ፍን አመጣ፤ አን​ቀ​ላ​ፋም ፤ ከጎ​ኑም አጥ​ን​ቶች አንድ አጥ​ን​ትን ወስዶ ስፍ​ራ​ውን በሥጋ መላው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፤ አንቀላዳም ከጎኑም አንዲት እጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 2:21
7 Referencias Cruzadas  

የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት እየተቃረበ ሲሄድ አብራምን ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እነሆ፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ መጣበት።


ሰዎች ከባድ እንቅልፍ በሚይዛቸውና በሚያስጨንቅ የሌሊት ቅዠት ጊዜ፥


ስለዚህም ዳዊት ጦሩንና ውሃ መቅጃውን ከሳኦል ራስጌ አንሥቶ እርሱና አቢሳ ከዚያ ሄዱ፤ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከባድ እንቅልፍ ልኮባቸው ተጫጭኖአቸው ተኝተው ስለ ነበር ይህ ሁሉ ሲሆን ማንም ነቅቶ ያየና ያወቀ አልነበረም።


እርሱም በሚናገርበት ጊዜ ኅሊናዬን ስቼ በግንባሬ ወደ መሬት ተደፋሁ፤ እርሱ ግን ዳሰሰኝና ከመሬት አንሥቶ በእግሮቼ አቆመኝ።


በሌሊት ሰዎች በአልጋ ላይ ተኝተው አፍላ እንቅልፍ ይዞአቸው ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕልምና በራእይ ይናገራል።


ስንፍና እንቅልፍን ያስከትላል፤ ስለዚህም ሰነፍ ሰው ይራባል።


ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios