1 ሳሙኤል 24:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፣ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፥ ከዋሻውም ወጣ፥ ከሳኦልም በኋላ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ብሎ ጮኸ፥ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፥ ዳዊትም ወደ ምድር ተጎንብሶ እጅ ነሣ። |
እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር።
ሳኦልም የዳዊትን ድምፅ ለይቶ ስላወቀ “ዳዊት ልጄ ሆይ! በእርግጥ ይህ ቃል የአንተ ነውን?” ሲል ጠየቀ። ዳዊትም “አዎ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ድምፄ ነው ሲል መለሰ።
እርሱም “መልኩ ምንን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እነሆ፥ ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየተነሣ ነው” ስትል መለሰችለት። ሳኦልም ያ ሳሙኤል መሆኑን ዐውቆ ስለ ክብሩ በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።