የኢያቡስቴንም ራስ በኬብሮን ለነበረው ለንጉሥ ዳዊት ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፤ “ሊገድልህ ይመኝ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ ንጉሥ ሆይ፥ ዛሬ በሳኦልና በቤተሰቡ ላይ እግዚአብሔር ለጌታዬ ለንጉሡ ተበቅሎለታል።”
1 ሳሙኤል 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተከታዮቹም ዳዊትን “እነሆ፥ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልሃል! እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ እንደሚጥልልህ ነግሮሃል፤ እነሆ፥ አሁን በጠላትህ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ!” አሉት፤ ዳዊትም በልቡ እየተሳበ በመቅረብ ሳኦል ሳያውቅ ከልብሱ ጫፍ ላይ ቈርጦ ወሰደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፣ “እግዚአብሔር፣ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቈርጦ ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፥ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች ወጣ፤ በዚያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ወደዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ሰዎች፦ እነሆ፥ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ በዓይንህም ደስ የሚያሰኝህን ታደርግበታለህ ብሎ እግዚአብሔር የነገርህ ቀን፥ እነሆ፥ ዛሬ ነው አሉት። ዳዊትም ተነሥቶ የሳኦልን መጎናጸፊያ ዘርፍ በቀስታ ቆረጠ። |
የኢያቡስቴንም ራስ በኬብሮን ለነበረው ለንጉሥ ዳዊት ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፤ “ሊገድልህ ይመኝ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ ንጉሥ ሆይ፥ ዛሬ በሳኦልና በቤተሰቡ ላይ እግዚአብሔር ለጌታዬ ለንጉሡ ተበቅሎለታል።”
ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤
“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”
ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቀዒላ መምጣቱ በተነገረው ጊዜ “እግዚአብሔር እርሱን በእጄ ሊጥልልኝ ነው፤ ዳዊት የግንብ ቅጽርና የተመሸጉ የቅጽር በሮች ወዳሉአት ከተማ በመዝለቁ ራሱን በወጥመድ ውስጥ አስገብቶአል” አለ።
ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤
ታማኞች ለሆኑ ለደጋግ ሰዎች የመልካም ሥራቸውን ዋጋ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ ጥሎልኝ ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔር መርጦ ያነገሠህን አንተን ልጐዳ አልፈለግሁም።