La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 24:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ፥ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤልም መንግሥት በአንተ አገዛዝ ሥር ጸንቶ እንደሚኖር ዛሬ አረጋግጫለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ አንተ በርግጥ እንደምትነግሥና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደምትጸና ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጉዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ማን ነው? ዛሬ ስላደረግህልኝ ቸርነት ጌታ ይመልስልህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጠላ​ቱን ተቸ​ግሮ አግ​ኝቶ በመ​ል​ካም መን​ገድ ሸኝቶ የሚ​ሰ​ድድ ማን ነው? ስለ​ዚህ ለእኔ ስላ​ደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ይመ​ል​ስ​ልህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም፥ እነሆ፥ አንተ በእርግጥ ንጉሥ እንድትሆን የእስራኤልም መንግሥት በእጅህ እንድትጸና እኔ አውቃለሁ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 24:20
12 Referencias Cruzadas  

“ይህም የሚሆነው እጁን በእግዚአብሔር ላይ አነሣ፤ ሁሉን የሚችለውንም አምላክ ተዳፈረ።


ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ! እስከ ሞት ድረስ ይርገጠኝ በአቧራም ላይ ጥሎ ክብር ያሳጣኝ!


ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤


የከዋክብት ተመራማሪዎቹ ከሄዱ በኋላ፥ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፥ “ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ስለሚፈልገው፥ ተነሥና ሕፃኑን ከእናቱ ጋር ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ቈይ” አለው።


ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።


እግዚአብሔር ላደረግሽው በጎ ነገር ዋጋሽን ይክፈልሽ! የእርሱን ጥበቃ ተማምነሽ የመጣሽው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ዋጋሽን የተትረፈረፈ ያድርገው!”


አሁን ግን መንግሥትህ ዘላቂ አይሆንም፤ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው መርጦአል፤ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ ስላልጠበቅህ እርሱን በሕዝቡ ላይ መሪ ይሆን ዘንድ ቀብቶታል።”


“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”


ሳኦልም ዳዊትን “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ነገርን ታደርጋለህ፤ ይሳካልሃልም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደ ፈለገበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።