Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማቴዎስ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የከዋክብት ተመራማሪዎቹ ከሄዱ በኋላ፥ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፥ “ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ስለሚፈልገው፥ ተነሥና ሕፃኑን ከእናቱ ጋር ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ቈይ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ጠቢባኑ ከሄዱ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣ “ተነሥ! የምትመለስበትን ጊዜ እስካስታውቅህ ድረስ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ በመሸሽ በዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻልና” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነርሱ ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና ተነሥ፥ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 2:13
29 Referencias Cruzadas  

ከሞት የተረፉት ሀዳድና ወደ ግብጽ ሸሽተው የሄዱ ጥቂቶች ኤዶማውያን የአባቱ አገልጋዮች ብቻ ነበሩ፤ በዚያን ጊዜ ሀዳድ ገና ሕፃን ነበር፤


በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው።


በሌሊት ሰዎች በአልጋ ላይ ተኝተው አፍላ እንቅልፍ ይዞአቸው ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕልምና በራእይ ይናገራል።


በዚህ ዐይነት ሰዎች ኃጢአት ከመሥራት እንዲቈጠቡ ያደርጋል፤ ትዕቢትንም ከእነርሱ ያስወግዳል።


ከዚህም በኋላ ንጉሡ “ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ እያነሣችሁ ዓባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፤ ሴቶች ልጆች ግን በሕይወት ይኑሩ” ሲል ለሕዝቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ።


ነገር ግን ይህን ነገር ሲያስብ ሳለ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “የዳዊት ዘር ዮሴፍ ሆይ! እጮኛህ ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ስለ ሆነ፥ እርስዋን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ።


በአንድ ከተማ መከራ ሲያበዙባችሁ፥ ወደ ሌላው ሽሹ፤ በእውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞች ሁሉ አታዳርሱም።


ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ እግዚአብሔር በሕልም ስላስጠነቀቃቸው፥ ተመራማሪዎቹ በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ተመልሰው ሄዱ።


ስለዚህ ዮሴፍም በሌሊት ተነሣና፥ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር ይዞ፥ ወደ ግብጽ ሄደ።


ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።


ነገር ግን አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ምትክ በይሁዳ ምድር ላይ መንገሡን በሰማ ጊዜ፥ ዮሴፍ ወደዚያ መሄድ ፈራ። ሆኖም በሕልም መመሪያ ስለ ተሰጠው፥ ወደ ገሊላ ምድር ሄደ።


እነርሱም “እኛ የመጣነው ከመቶ አለቃው ከቆርኔሌዎስ ዘንድ ነው፤ እርሱ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ የሚያከብረው እግዚአብሔርን የሚያመልክ ደግ ሰው ነው፤ አንተን ወደ ቤቱ አስጠርቶ የምትለውን እንዲሰማ ቅዱስ መልአክ ገልጦ ነግሮታል” አሉት።


ይህን የነገረው መልአክ ተለይቶት በሄደ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ከአገልጋዮቹ ሁለቱንና የእርሱ ክፍል ከሆኑት ወታደሮች እግዚአብሔርን የሚፈራውን አንዱን ጠራና፥


ጴጥሮስም ወደ ልቡናው ተመልሶ፥ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠባበቁት ከነበረው ነገር ሁሉ ያዳነኝ መሆኑን አሁን ገና በእውነት ዐወቅሁ!” አለ።


በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ ተገልጦ ታየ፤ በወህኒ ቤቱም ውስጥ ብርሃን በራ፤ መልአኩ የጴጥሮስን ጐን መትቶ ቀሰቀሰውና “በፍጥነት ተነሥ!” አለው፤ ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ላይ ወደቁ።


የወህኒ ቤት ጠባቂውም “እናንተ እንድትለቀቁ ባለሥልጣኖቹ ሰው ልከዋልና እንግዲህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ሲል ለጳውሎስ ነገረው።


የእግዚአብሔር መልአክ ግን በሌሊት የወህኒ ቤቱን በሮች ከፍቶ፥ አስወጣቸውና፥


አዲሱ ንጉሥ በሕዝባችን ላይ በተንኰል ተነሥቶ አባቶቻችንን ይጨቊናቸው ጀመር፤ ሕፃኖቻቸውም እንዲሞቱና ወደ ውጪ አውጥተው እንዲጥሉአቸው፥ አባቶቻችንን አስገደዳቸው።


የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች ውሃውን በሚነኩበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መውረዱን ያቆማል፤ ከላይ እየጐረፈ የሚመጣውም ውሃ በአንድ ቦታ ተሰብስቦ ይቈለላል።”


ሕዝቡ በደረቅ ምድር እየተራመዱ በሚሻገሩበት ጊዜ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ተሻግረው እስካበቁ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቅ ምድር ላይ ቆመው ነበር።


ለሕዝቡ እንዲነግር እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ሁሉ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ካህናቱ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል እንደ ቆሙ ቈዩ፤ ሙሴም ኢያሱን ያዘዘው ይህንኑ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥኖ ወንዙን ተሻገሩ።


የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ወጥተው እግሮቻቸው ደረቁን መሬት በረገጡ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ ወደ ቦታው ተመልሶ እንደ ቀድሞው ሞልቶ ይፈስ ጀመር።


ሴቲቱ በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ የታላቅ ንስር ክንፎች የሚመስሉ ሁለት ክንፎች ተሰጡአት፤ እዚያም ከእባቡ ፊት ርቃ ሦስት ዓመት ተኩል በእንክብካቤ ተይዛ ትጠበቅ ነበር።


በጅራቱ የኮከቦችን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣላቸው፤ ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ልጅዋን ለመዋጥ አስቦ ዘንዶው ልትወልድ ወደተቃረበችው ሴት ከፊት ለፊትዋ ቆመ፤


ሴቲቱም ወደ በረሓ ሸሽታ ሄደች፤ እዚያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን በእንክብካቤ ተይዛ የምትጠበቅበትን ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶላት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos