La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ሳኦል በእስራኤል ምርጥ የሆኑትን ሦስት ሺህ ወታደሮች በማስከተል “የሜዳ ፍየሎች አለት” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ዳዊትን አሳዶ ለመያዝ ሄደ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺሕ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዐለት” ወደተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፥ “እነሆ፥ ዳዊት በዔንገዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገሩት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ከተ​መ​ለሰ በኋላ፥ “እነሆ! ዳዊት በዓ​ይን ጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገ​ሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ የበረሀ ፍየሎች ወደ ነበሩባቸው ዓለቶች ሄደ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 24:2
9 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬ የደኅንነቴ ኀይል፥ ጠንካራ ምሽጌ ነው።


“የበረሓ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋልያ አምጣ ስትወልድ አይተህ ታውቃለህን?


ዋልያዎች በከፍተኛ ተራራዎች ላይ ይገኛሉ፤ ሽኮኮዎችም በተሰነጠቁ አለቶች ውስጥ ይኖራሉ።


ዳኞቻቸው በገደል አለት ላይ በተጣሉ ጊዜ ሕዝቦቻቸው የእኔ ቃል እውነት መሆኑን ያረጋግጣሉ።


ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል።


ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።


ከእስራኤል ሕዝብ መካከል የተውጣጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን መረጠ፤ ከእነርሱ መካከል ሁለቱን ሺህ በሚክማስና በቤትኤል በሚገኘው ኮረብታማ አገር ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ መደበ፤ አንዱን ሺህ ሰዎች ደግሞ ከልጁ ከዮናታን ጋር በማሰለፍ በብንያም ነገድ ግዛት ውስጥ ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ኮረብታማ አገር ላከ፤ ከዚህ የተረፉትን ሌሎች ሰዎች ግን ወደየቤታቸው አሰናበተ።


ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው።


ሳኦልም በፍጥነት ተነሥቶ በእስራኤል ምርጥ የሆኑትን ሦስት ሺህ ወታደሮች በማስከተል ዳዊትን ለመፈለግ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ሄደ፤