ሣራይም አብራምን “የደረሰብኝ በደል በአንተ ላይ ይሁን፤ እርስዋን ለአንተ የሰጠሁህ እኔ ራሴ ነኝ፤ እርስዋ ግን መፅነስዋን ካወቀችበት ጊዜ አንሥቶ እኔን መናቅ ጀምራለች፤ አሁንም ከእኔና ከአንተ ጥፋተኛው ማን እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይፍረድ!” አለችው።
1 ሳሙኤል 24:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ስሕተተኛው ማንኛችን እንደ ሆንን በመለየት እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ! እኔ በአንተ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስብህ ስለማልፈልግ በእኔ ላይ ስለምታደርገው ክፉ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ ይበቀል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ይፍረድ። ክፉ ስላደረግህብኝ እግዚአብሔር ይበቀልህ እንጂ፣ እጄስ በአንተ ላይ አትሆንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቴ ሆይ፤ የልብስህ ቁራጭ ይኸው በእጄ ላይ ተመልከተው! የልብስህን ጫፍ ቆረጥሁ እንጂ አንተን አልገደልኩህም። አሁንም ክፋት ወይም ዐመፅ አለመፈጸሜን ዕወቅልኝ፤ ተረዳልኝም፤ እኔ ክፉ አልሠራሁብህም፤ አንተ ግን ሕይወቴን ለማጥፋት እያሳደድኸኝ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ ዕወቅ፤ የልብስህንም ዘርፍ በቈረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፤ ስለዚህም በእጄ ክፋት፥ በደልና ክዳት እንደሌለ፥ አንተንም እንዳልበደልሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍሴን ልታጠፋ ታጠምዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፥ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፥ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም። |
ሣራይም አብራምን “የደረሰብኝ በደል በአንተ ላይ ይሁን፤ እርስዋን ለአንተ የሰጠሁህ እኔ ራሴ ነኝ፤ እርስዋ ግን መፅነስዋን ካወቀችበት ጊዜ አንሥቶ እኔን መናቅ ጀምራለች፤ አሁንም ከእኔና ከአንተ ጥፋተኛው ማን እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይፍረድ!” አለችው።
ይህንን ሳናደርግ ብንቀር ግን ከአብርሃም አምላክ፥ ከናኮር አምላክና ከአባታቸውም አምላክ ቅጣት ይድረስብን።” ከዚህ በኋላ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ በሚያመልከው አምላክ ስም ይህን ቃል ለመጠበቅ ማለ።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።
ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።
እኔ በበኩሌ ምንም አልበደልኩም፤ በእኔ ላይ ጦርነት በመክፈት ልትበድለኝ የተነሣሣህ አንተ ነህ፤ እንግዲህ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ዛሬ በእስራኤላውያንና በዐሞናውያን መካከል ውሳኔ ይሰጣል።”
ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት በመሸሽ ወደ ዮናታን ሄዶ “ከቶ ምን አደረግሁ? ምንስ ወንጀል ፈጸምኩ? አባትህ ለመግደል የሚፈልገኝስ ምን በድየው ነው?” ሲል ጠየቀው።
እግዚአብሔር ይፍረድ፤ ከሁለታችንም ስሕተተኛው ማን እንደ ሆነ እርሱ ይወስን፤ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ይከላከልልኝ፤ ከአንተም እጅ ያድነኝ።”
ታማኞች ለሆኑ ለደጋግ ሰዎች የመልካም ሥራቸውን ዋጋ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ ጥሎልኝ ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔር መርጦ ያነገሠህን አንተን ልጐዳ አልፈለግሁም።