1 ሳሙኤል 22:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሳኦል የካህናት ከተማ በሆነችው በኖብ የሚኖሩት ሁሉ ወንዶችና ሴቶች፥ ልጆችና ሕፃናት፥ የቀንድ ከብቶችና አህዮች፥ እንዲሁም የበግ መንጋዎች ሁሉ እንዲገደሉ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፣ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፣ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፣ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፣ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፥ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፥ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፥ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት አስገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፤ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም፥ በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናቱም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፥ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ። |
በሕዝባችሁ ላይ ከባድ ጦርነት ይመጣል፤ ምሽጎቻችሁ ሁሉ ይፈራርሳሉ፤ ይህም ንጉሥ ሸልማን የቤትአርቤልን ከተማ በጦርነት እንዳፈራረሰና እናቶችን ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ ፈጥፍጦ እንደ ጨረሰበት ጊዜ ይሆናል።
ስለዚህ ኢየሱስን “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት፤ እርሱም “አዎ፥ እሰማለሁ፤ ‘ከልጆችና ከሚጠቡት ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው፤
“በከተማይቱና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር የተረገመ ሆኖ መደምሰስ አለበት፤ ሴትኛ ዐዳሪዋ ግን የላክናቸውን ሰላዮች ደብቃ ስላዳነች መትረፍ የሚገባቸው እርስዋና ከእርስዋ ጋር በቤትዋ ያሉት ብቻ ናቸው።
ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”
ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ የአጋግን ሕይወት አተረፉ፤ እንዲሁም ምርጥ ምርጥ የሆኑትን በጎችና የቀንድ ከብቶች፥ የሰቡ ሰንጋዎችንና ጠቦቶችን ከዚህም ጋር መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አላጠፉም፤ እነርሱም ያጠፉት የማይረባውንና የማይጠቅመውን ነገር ብቻ ነበር።
ዳዊት በኖብ ወደሚገኘው ወደ ካህኑ አቤሜሌክ ዘንድ ሄደ፤ አቤሜሌክም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ሊቀበለው ወጥቶ “ማንም ሰው ሳይከተልህ ብቻህን ስለምን ወደዚህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው።
ስለዚህም ንጉሥ ሳኦል ወደ ካህኑ የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክና በኖብ ወደሚገኙት ዘመዶቹ ወደሆኑት ካህናት ሁሉ መልእክት ላከ፤ እነርሱም መጡ፤
በዚህን ጊዜ ከባለሥልጣኖቹ ጋር ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ቆሞ ስለ ነበር “እኔ የእሴይን ልጅ በኖብ ወደሚገኘው የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክ በመጣ ጊዜ አይቼዋለሁ፤