1 ሳሙኤል 20:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወት ብኖር እግዚአብሔር የሚወድደውን ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ብሞት ግን እግዚአብሔር የአንተን የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ ከገጸ ምድር በሚያጠፋበት ጊዜ ታማኝ የሆነውን ፍቅርህን ከቤተሰቤም አታቋርጥ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም እኔ በሕይወት እስካለሁ ድረስ እንዳልገደል የእግዚአብሔርን በጎነት አድርግልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እንዳልሞት፥ በሕይወት እስካለሁ የጌታን ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በሕይወት ሳለሁ ቸርነትን ታደርግልኛለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እንዳልሞት በሕይወቴ ዘመን የእግዚአብሔርን ቸርነት አድርግልኝ፥ |
ንጉሡም “እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ቸርነት የማሳየው ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ሲል ጺባን ጠየቀው። ጺባም “ከዮናታን ወንዶች ልጆች አንዱ አሁንም በሕይወት አለ፤ እርሱም እግረ ሽባ ነው” ሲል መለሰ።
አንተን ለመጒዳት የሚፈልግ ከሆነ ግን፥ ስለ እርሱ ባልገልጥልህና አንተም በሰላም እንድታመልጥ ባላደርግ አባቴ በአንተ ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ክፉ ነገር እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያድርሰው። እግዚአብሔር ከአባቴ ጋር እንደ ነበር ከአንተም ጋር ይሁን፤