La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 19:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊትም አምልጦ ሳሙኤል ወደነበረበት ወደ ራማ መጣ፤ ሳኦል ያደረገበትንም በደል ሁሉ ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤልና ዳዊት በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ሸሽቶ ካመለጠ በኋላ፣ ወደ አርማቴም ወደ ሳሙኤል ሄደ፣ ሳኦል ያደረገበትን ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ወደ ነዋት ሄደው ተቀመጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ሸሽቶ ካመለጠ በኋላ፥ ወደ ራማ ወደ ሳሙኤል ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትን ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ሸሽቶ አመ​ለጠ፤ ወደ አር​ማ​ቴ​ምም ወደ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ሁሉ ነገ​ረው፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሄዱ፤ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራ​ማም ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፥ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፥ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ በነዋትዘራማም ተቀመጡ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 19:18
11 Referencias Cruzadas  

በፍርሃቴ ጊዜ እንኳ “ማንም የሚታመን የለም” አልኩ።


ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤


በማግስቱም ሕልቃናና ቤተሰቡ በማለዳ ተነሥተው ለእግዚአብሔር ከሰገዱ በኋላ በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ሄዱ፤ ሕልቃናም ከሚስቱ ከሐና ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እግዚአብሔርም አስታወሳት፤


ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፤ ንጉሥ ሳኦልም ወደ ጊብዓ ተመለሰ።


ዳዊት በራማ በምትገኘው በናዮት መኖሩን ሳኦል ሰማ፤


ከዚህ በኋላ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ለመሄድ ተነሣ፤ እዚያም ሴኩ በሚባለው ስፍራ ወደሚገኘው ወደ አንድ ታላቅ የውሃ ጒድጓድ በደረሰ ጊዜ “ሳሙኤልና ዳዊት የሚገኙት የት ነው?” ብሎ ቢጠይቅ፥ በናዮት መኖራቸው ተነገረው።


ወደዚያም በማምራት ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ወረደበት፤ እስከ ናዮት በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ትንቢት ይናገር ነበር፤


ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት በመሸሽ ወደ ዮናታን ሄዶ “ከቶ ምን አደረግሁ? ምንስ ወንጀል ፈጸምኩ? አባትህ ለመግደል የሚፈልገኝስ ምን በድየው ነው?” ሲል ጠየቀው።


የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖች “ይህ በአገሩ የነገሠው ዳዊት አይደለምን? ‘ሳኦል ሺህ ገዳይ! ዳዊት ዐሥር ሺህ ገዳይ!’ እያሉ ሴቶች በጭፍራ የዘፈኑለት እርሱ አይደለምን?” ሲሉ አኪሽን ጠየቁት።


እነሆ፥ ሳሙኤል ከሞተ ቈየት ብሎአል፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ለእርሱ በማዘን አልቅሰው በሚኖርባት በራማ ቀብረውታል፤ ቀደም ሲል ሳኦል ጠንቋዮችንና ሙታን ጠሪዎችን ከእስራኤል ምድር እንዲባረሩ አስገድዶአቸው ነበር።


ከዚያም በራማ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየተመለሰ እዚያም የዳኝነት ሥራ ይሠራ ነበር፤ በዚህም በራማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።