ከበጎችህ አንዱን አውሬ ሲበላው ወዲያው እከፍልህ ነበር እንጂ የእኔ ስሕተት ያለመሆኑን ለማስረዳት ወደ አንተ አምጥቼው አላውቅም፤ በቀንም ቢሆን በሌሊት የተሰረቀ እንስሳ ቢኖር ታስከፍለኝ ነበር።
1 ሳሙኤል 17:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ ያንተ አሽከር የአባቴን በጎች የምጠብቅ እረኛ ነኝ፤ አንበሳም ሆነ ድብ መጥቶ ጠቦት በሚነጥቅበት ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ግን ሳኦልን እንዲህ አለው፣ “አገልጋይህ የአባቱን በጎች በሚጠብቅበት ጊዜ፤ አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው አንድ በግ ነጥቆ ሲሄድ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ግን ሳኦልን እንዲህ አለው፥ “አገልጋይህ የአባቱን በጎች በሚጠብቅበት ጊዜ፤ አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው አንድ በግ ነጥቆ ሲሄድ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሳኦልን አለው፥ “እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመንጋውም ጠቦት ይወስድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሳኦልን አለው፦ እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር፥ ከመንጋውም ጠቦት ይወስድ ነበር። |
ከበጎችህ አንዱን አውሬ ሲበላው ወዲያው እከፍልህ ነበር እንጂ የእኔ ስሕተት ያለመሆኑን ለማስረዳት ወደ አንተ አምጥቼው አላውቅም፤ በቀንም ቢሆን በሌሊት የተሰረቀ እንስሳ ቢኖር ታስከፍለኝ ነበር።
አባትህ ዳዊትና ተከታዮቹ ብርቱ ጦረኞች እንደሆኑና ግልገሎችዋ እንደ ተነጠቁባትም ድብ አስፈሪዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፤ አባትህ በጦር ልምድ የተፈተነ ወታደር በመሆኑ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤
ሌላው ዝነኛ ወታደር የቃብጽኤል ተወላጅ የነበረው የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ እርሱም ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ወታደሮችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤
በቃብጽኤል ምድር የዮዳሄ ልጅ በናያ ዝነኛ ወታደር ነበር፤ እርሱ ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ጦረኞችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤
የበግ እረኞች ከተበታተኑት በጎቻቸው መካከል መንጋዎቻቸው እንደሚፈለጉ፥ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበታተኑበት ቦታ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሰማርያ የሚኖሩ እስራኤላውያን ከአልጋና ከድንክ አልጋ ቊራጭ ጋር ያመልጣሉ፤ ይኸውም እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ ሁለት እግርና የጆሮ ቊራጭ ለማስጣል እንደሚችለው ዐይነት ነው።”
እነሆ በምድሪቱ መንጋዬን የሚጠብቅ አንድ እረኛ አስነሣለሁ፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እርሱ ስለ ጠፉት አያስብም፤ የባዘኑትን አይፈልግም፤ ያነከሱትን አይፈውስም፤ ጤናማዎችንም አይመግብም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የወፈረውን እያረደ ይበላል፤ ሰኮናቸውንም ይቈራርጣል።
ከእንግዲህ ወዲህ ደም ያለበትን ጥሬ ሥጋ ወይም ማንኛውንም የተከለከለ ምግብ አይበሉም፤ ከእነርሱ የተረፉት ከሕዝቤ ተቀላቅለው ከይሁዳ ነገድ እንደ አንድ ጐሣ ይሆናሉ፤ የዔቅሮን ሕዝብ ልክ እንደ ኢያቡሳውያን ከሕዝቡ ጋር ይቀላቀላሉ።
ያየሁት አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፥ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው።
በድንገትም የእግዚአብሔር መንፈስ ሶምሶንን አበረታው፤ ስለዚህም አንበሳውን እንደ አንድ የፍየል ጠቦት ያኽል በመቊጠር ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጥሎ ጣለው፤ ያደረገውንም ነገር ለወላጆቹ አልነገራቸውም።
ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።
ተከትዬው ሄጄ አደጋ በመጣል የወሰደውን ጠቦት አስጥለው ነበር፤ አንበሳው ወይም ድቡ ወደ እኔ ተመልሶ በሚመጣበትም ጊዜ ጉሮሮውን አንቄ በመምታት እገድለው ነበር።