እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
1 ሳሙኤል 17:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃው የጦር አዛዥ ስጠው፤ ወንድሞችህም እንዴት እንዳሉ በዐይንህ አይተህ የደኅንነታቸውን መረጃ አምጣልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለክፍል አዛዣቸው ዐብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፣ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለሻለቃው የጦር አዛዥ አብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፥ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ዐሥሩን አይብ ወደ ሻለቃው ውሰደው፤ የወንድሞችህንም ደኅንነት ጠይቅ፤ ወሬአቸውንም አምጣልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም አሥሩን አይብ ወደ ሻለቃው ውሰደው፥ የወንድሞችህንም ደኅንነት ጠይቅ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ። |
እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
አባቱም “በል እንግዲህ ሂድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዐይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም ደረሰ።
መርዶክዮስም አስቴር በምን ሁኔታ እንዳለችና ወደ ፊት የሚገጥማት ዕድል ምን እንደሆን ለማወቅ በየቀኑ በምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት አደባባይ ፊት ለፊት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር።
ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው።
ዳዊትም ደክሞአቸው በብሦር ምንጭ አጠገብ ዕረፍት በማድረግ ቈይተው ወደነበሩት ወደ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ተመልሶ ሄደ። እነርሱም ዳዊትንና ተከታዮቹን ሊቀበሉአቸው መጡ፤ ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ ደኅንነታቸውን በመጠየቅ ሰላምታ አቀረበላቸው።