1 ሳሙኤል 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖስም “ከእናንተ ጋር የውል ስምምነት ማድረግ የምችልበት አንድ ዐይነት ግዴታ አለ፤ ይኸውም የእያንዳንዱን ሰው ቀኝ ዐይን በማውጣት በእስራኤላውያን ላይ አሳፋሪ ውርደት አመጣለሁ” ሲል መለሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናዊው ናዖስ፣ “ከእናንተ ጋራ ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናዊው ናዖስ ግን፥ “ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞናዊው ናዖስም፦“ ቀኝ ዐይናችሁን ብታወጡ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብን አደርጋለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞናዊውም ናዖስ፦ ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ በማውጣት ቃል ኪዳን አደርግላችኋለሁ፥ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብ አደረጋለሁ አላቸው። |
ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤
እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።
ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!”
ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤
እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ንጉሣችሁ ሆኖ ሳለ የአሞን ንጉሥ ናዖስ በእናንተ ላይ መነሣቱን ባያችሁ ጊዜ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ።
ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እስራኤልን ከዚህ አሳፋሪ ውርደት ለሚያድን ሰው ምን ይደረግለታል? ኧረ ለመሆኑ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት የሚፈታተን ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።