1 ሳሙኤል 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም አልፈህ በታቦር ወደሚገኘው ወደ አንድ ትልቅ ዛፍ ትደርሳለህ፤ እዚያም ወደ ቤትኤል ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ ሦስት ሰዎችን ታገኛለህ፤ ከእነርሱ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶችን እየሳበ የሚሄድ ሲሆን ሁለተኛው ሰው ሦስት ኅብስት የተሸከመ ነው፤ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ የተሸከመ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተም ጕዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፣ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፣ ሌላው ሦስት ዳቦ፣ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቍማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተም ጉዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው ባሉጥ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፥ ሌላው ሦስት ዳቦ፥ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ደግሞ አልፈህ፥ ወደ ትልቁ የታቦር ዛፍ ትደርሳለህ፤ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች ሲነዳ፥ ሁለተኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገኛለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ደግሞ ወደ ፊት ትሄዳለህ፥ ወደ ታቦር ወደ ትልቁ ዛፍ ትደርሳለህ፥ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች፥ ሁለተኛው ሦስት ዳቦ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል፥ |
እግዚአብሔር ያዕቆብን “አሁን ተነሥተህ ወደ ቤትኤል ሂድና እዚያ ኑር፤ በዚያም ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድክ ጊዜ ለተገለጥኩልህ አምላክ ለእኔ መሠዊያ ሥራ” አለው።
ከዚህ ተነሥተን ወደ ቤትኤል እንውጣ፤ በዚያም ከዚህ በፊት በተቸገርኩ ጊዜ ጸሎቴን ሰምቶ ለረዳኝና በሄድኩበት ስፍራ ሁሉ ከእኔ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”
እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሐናምኤል ታስሬ ወዳለሁበት ወደ ዘብ ጠባቂዎች ክፍል መጥቶ “የመግዛት መብት ያንተ ስለ ሆነ መሬቴን ግዛ” አለኝ፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ ዐወቅሁ።
ከእርሱም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት የምግብ መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ ይህም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል፤ ከዚህም ጋር አንድ ሊትር የሚሆን የወይን ጠጅ ስጦታ ታቀርባላችሁ።
ድንበሩም መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ፥ ከታቦር፥ ከሻሐጹማና ከቤትሼሜሽ ጋር ይዋሰናል፤ እርሱም ዐሥራ ስድስት ከተሞችንና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል፤
እስራኤላውያን ወደ ቤትኤል ወጥተው “በብንያማውያን ላይ መጀመሪያ አደጋ መጣል የሚገባው የትኛው ነገድ ነው?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “የይሁዳ ነገድ አስቀድሞ ይዝመት” አላቸው።
እስራኤላውያንም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንዝመትን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፦ “አዎ፥ በእነርሱ ላይ ዝመቱ” አላቸው።
የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤
ከዚህ በኋላ ጌዴዎን “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” ሲል ዜባሕንና ጻልሙናዕን ጠየቀ። እነርሱም “አንተን ይመስሉ ነበር፤ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት።