1 ሳሙኤል 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሊም “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምልክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊም፣ “በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ” ሲል መለሰላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዔሊ፥ “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም፥ “በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤልም አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን የለመንሽውንም ልመና ሁሉ ይስጥሽ” ብሎ መለሰላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም፦ በደኅና ሂጂ፥ የእስራኤልም አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ ብሎ መለሰላት። |
ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
ሕልቃናም “ጥሩ ነው፤ መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይውም ድረስ በቤት መቈየት ትችያለሽ፤ እግዚአብሔር የሰጠሽን የተስፋ ቃል ይፈጽምልሽ” ሲል መለሰላት፤ ስለዚህም ሐና በቤት ተቀምጣ ልጇን ታሳድግ ጀመር።
ከዚህ በኋላ ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በሰላም ሂድ፤ እኔና አንተ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል።” ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
ከዚያም በኋላ ዳዊት ያመጣችለትን ስጦታ ተቀብሎ “ወደ ቤትሽ በሰላም ተመልሰሽ ሂጂ፤ ልመናሽን ሰምቼአለሁ፤ የጠየቅሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አላት።