እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አሁን ተነሥተህ ከኀያሉ ታቦትህ ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ና፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በበረከትህ ይደሰቱ፤
1 ጴጥሮስ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አሁን ተነሥተህ ከኀያሉ ታቦትህ ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ና፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በበረከትህ ይደሰቱ፤
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።
በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ።
እናንተ ግን እንደ እነርሱ ልትሆኑ አይገባም፤ ይልቅስ ከእናንተ መካከል ትልቅ የሆነ እንደ ትንሽ ይሁን፤ አለቃ የሆነም እንደ አገልጋይ ይሁን።
በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ በሥልጣናቸውም ሥር ሁኑ፤ እነርሱ የሚጠየቁበት ኀላፊነት ስላለባቸው ስለ ነፍሳችሁ ጉዳይ ይተጋሉ፤ እናንተ ብትታዘዙአቸው እነርሱ ሥራቸውን በደስታ ያከናውናሉ፤ ያለበለዚያ ሥራቸውን በሐዘን ይሠራሉ፤ ይህም እናንተን የሚጠቅም አይሆንም።
በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።
ክርስቶስ በሥጋው መከራ የተቀበለ ስለ ሆነ እናንተም የጦር መሣሪያን እንደ ታጠቀ ሰው በዚህ ሐሳብ በርትታችሁ ተዘጋጁ፤ በሥጋው መከራን የተቀበለ ሰው ኃጢአት መሥራትን አቋርጧል።