ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈጽሞታል።”
1 ነገሥት 8:56 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሰጠው ተስፋ መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን ለሰጠ እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ በባሪያው በሙሴ አማካይነት ከተሰጠው መልካም ተስፋ ሁሉ አንድም ቃል አልቀረምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፥ በባሪያው በሙሴ ቃል ከተናገረው ከመልካም ቃል ሁሉ ያጐደለው አንድም ቃል የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን! በባሪያው በሙሴ ከሰጠው ከመልካም ተስፋ ሁሉ አንድ ቃል አልወደቀም። |
ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈጽሞታል።”
ይሁን እንጂ እንዲህ በማለት የተስፋ ቃል ሰጥቶኛል፥ ‘እኔ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፌ ሰላም ስለምሰጠው በሰላም የሚያስተዳድር ወንድ ልጅ ይኖርሃል፤ በእርሱ ዘመነ መንግሥት ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ ስለምሰጥ ስሙ ሰሎሞን ተብሎ ይጠራል፤
እንዲህም አለ፥ “ከግብጽ ንጉሥና ከሕዝቡም እጅ ያዳናችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡንም ከባርነት ነጻ ያወጣ እግዚአብሔር ይመስገን!
እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ምድር ለመኖር ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፤ በደኅና እንድትኖሩ በዙሪያ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ዕረፍት ይሰጣችኋል፤
እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።
እግዚአብሔር ለእናንተ በዚህ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ለእነርሱም ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ በኩል የሚያወርሳቸውን ምድር ሰጥቶ በሰላም እስካሳረፋቸው ድረስ ወገኖቻችሁን እስራኤላውያንን እርዱ፤ ከዚያም በኋላ እኔ ወደ ሰጠኋችሁ ወደዚህች ምድር መመለስ ትችላላችሁ።’