የእያንዳንዳቸው ቁመት አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የሆነ፥ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ።
1 ነገሥት 6:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተከፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ የወይራ ዕንጨት ደጃፎች ሠራ፤ መቃኖቻቸውንና መድረኮቻቸውን ባለዐምስት ማእዘን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተከፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ሳንቃዎችን ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን፥ ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቅዱስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ደጆች ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ። |
የእያንዳንዳቸው ቁመት አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የሆነ፥ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ።
ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፥ ኪሩቤልን፥ የዘንባባ ዛፎቹን፥ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው።
የመብራት ማብሪያና ማጥፊያዎች፥ ማንቈርቈሪያዎች፥ ጥናዎችና የእሳት መጫሪያዎች፤ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ናቸው፤ የቤተ መቅደሱ የውጪ በሮችና የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ።