1 ነገሥት 22:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ሊጥሉበት ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም በጮኸ ጊዜ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሠረገላው አዛዦችም ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፣ “የእስራኤል ንጉሥ ይህ ነው” ብለው አሰቡ፤ ሊወጉትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ሊጥሉበት ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም በጮኸ ጊዜ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰረገሎች አለቆችም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፥ “በእውነት የእስራኤልን ንጉሥ ይመስላል፤” አሉ ይዋጉትም ዘንድ ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠረገሎች አለቆችም ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ “በእውነት የእስራኤል ንጉሥ ነው፤” አሉ፤ ይገጥሙትም ዘንድ ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም ጮኸ። |
ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከበቡት፤ ነገር ግን ኢዮሣፍጥ ጮኸ፤ እግዚአብሔር አምላክም ከእነርሱ እጅ በመታደግ አዳነው፤ እነርሱም በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተገቱ።