1 ነገሥት 13:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እየጋለበ ያን የእግዚአብሔር ሰው ተከተለው። ከዚያም በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘውና፣ “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ሰው የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የባሉጥ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ሰው ተከትሎት ሄደ፤ ከዛፍ በታችም ተቀምጦ አገኘውና፥ “ከይሁዳ የመጣህ የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እርሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔርም ሰው በኋላ ሄደ፤ በአድባርም ዛፍ በታች ተቀምጦ አገኘውና “ከይሁዳ የመጣህ የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እርሱም “እኔ ነኝ፤” አለ። |
ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ መንገድ ከመሄድ የተነሣ ስለ ደከመው በጒድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ።
ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል።