1 ነገሥት 1:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዶንያስም ሰሎሞንን ስለ ፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ የመሠዊያውን ቀንዶች በመያዝ ተማጠነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዶንያስ ግን ሰሎሞንን በመፍራት ሄዶ፣ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፥ ተነሥቶም ሄደ፥ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶንያስም ከሰሎሞን ፊት የተነሣ ፈራ፤ ተነሥቶም ሄደ፤ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፤ ተነሥቶም ሄደ፤ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ። |
ሰዎቹም ሰሎሞንን “አዶንያስ አንተን ከመፍራቱ የተነሣ የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ‘ከሁሉ በፊት ንጉሥ ሰሎሞን የማይገድለኝ መሆኑን በማረጋገጥ በመሐላ ቃል ይግባልኝ’ በማለት እየተማጠነ ነው” ሲሉ ነገሩት።
በአንድ በኩል የአዶንያስ ደጋፊ፥ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤሴሎም ተቃዋሚ የሆነው ኢዮአብ ይህን የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ፤
በአራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ጠርበህ ቀንድ መሳይ ጒጦች አውጣ፤ ይህም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠራ ይሁን፤ እርሱም በነሐስ የተለበጠ ይሁን።
አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።”
መሥዋዕቱ የሚቃጠልበት ይህ የላይኛው መጨረሻ እርከን አራት ክንድ ከፍታ ነበረው፤ በአራቱ ማእዘኖች ላይ ያሉት የመሠዊያው ቀንዶች ከመሠዊያው ጫፍ ላይ ካለው ክፈፍ በላይ ከፍ ያሉ ነበሩ።