1 ዮሐንስ 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእናንተ የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ እናንተስ እውነትን ታውቃላችሁ፤ በእውነትም ሐሰት እንደማይገኝ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእናንተ የምጽፍላችሁ እውነቱን ስለማታውቁት አይደለም፤ ነገር ግን ስለምታውቁት እና ምንም ውሸት ከእውነቱ ስላልሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለምታውቁትና ውሸት ሁሉ ከእውነት ስላልሆነ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም። |
ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።
ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።