የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና በመድፈሩም ምክንያት አቤሴሎም አምኖንን እጅግ ጠላው፤ ዳግመኛም ክፉም ሆነ ደግ ሊያነጋግረው አልፈለገም።
1 ዮሐንስ 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይኖራል፤ በጨለማም ይመላለሳል፤ ጨለማውም ዐይኑን ስላሳወረው የሚሄድበትን አያውቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፤ በጨለማ ይመላለሳል፤ ጨለማው ስላሳወረውም የት እንደሚሄድ አያውቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይኖራል፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ ጨለማው ዐይኖቹን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና። |
የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና በመድፈሩም ምክንያት አቤሴሎም አምኖንን እጅግ ጠላው፤ ዳግመኛም ክፉም ሆነ ደግ ሊያነጋግረው አልፈለገም።
ጥበበኞች ሰዎች መነሻና መድረሻቸውን ያውቃሉ፤ ሞኞች ግን ይህን ሁሉ አያውቁም፤” ይሁን እንጂ ጥበበኛም ሆነ ሞኝ ሁለቱም የሚኖራቸው ዕድል አንድ ዐይነት መሆኑን ተረዳሁ።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
የእነርሱ ልቡና በእርግጥ ደንዝዞአል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ሲያነብቡ ልቡናቸው በዚያው መሸፈኛ እንደ ተሸፈነ ነው። ይህም የሚሆነው ያ መሸፈኛ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ነው።
የዚህ ዓለም ገዢ የሆነው ሰይጣን የማያምኑትን ሰዎች ልብ አሳወረው፤ በዚህም በእግዚአብሔር መልክ የተገለጠው የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል የሚያበራላቸውን ብርሃን እንዳያዩ አደረጋቸው።
እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን።
ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት አለን” እያልን በጨለማ የምንኖር ከሆንን እንዋሻለን፤ በቃላችንም ሆነ በሥራችን እውነት የለም ማለት ነው።
‘እኔ ሀብታም ነኝ፤ ብዙ ሀብት አለኝ፤ የሚጐድለኝ ምንም የለም’ ትላለህ፤ ነገር ግን ጐስቋላ፥ ምስኪን፥ ድኻ፥ ዕውርና የተራቈትህ መሆንክን አታውቅም፤