1 ቆሮንቶስ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ የእግዚአብሔር የሆንን ዐብሮ ሠራተኞች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ዕርሻ፣ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። |
በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤ ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤ የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።
ምድር ቡቃያዎችን እንደምታበቅል፥ የአትክልት ቦታም ተክሎችን እንደምታሳድግ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ጽድቅና ምስጋና ከሕዝቦች ሁሉ ዘንድ እንዲፈልቁ ያደርጋል።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።
ደቀ መዛሙርቱም በየስፍራው ሁሉ እየሄዱ አስተማሩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር። ተአምራትንም የማድረግ ሥልጣን በመስጠት የትምህርታቸውን እውነተኛነት ያጸና ነበር።]
ሰውነታችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን ታውቁ የለምን? እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ እንጂ የራሳችሁ አይደላችሁም።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።
እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።
ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።