1 ቆሮንቶስ 16:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማችን አጵሎስ ከሌሎች ወንድሞች ጋር እናንተን እንዲጐበኛችሁ በጥብቅ ለምኜው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ አሁን ወደ እናንተ ለመምጣት አልፈቀደም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፣ ከወንድሞች ጋራ ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፥ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስም ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ መላልሼ ማልጄው ነበር፤ አሁን ሊመጣ አልወደደም፤ በተቻለው ጊዜ ግን ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ግን ከወንድሞቹ ጋር ወደ እናንተ ሊሄድ እጅግ አድርጌ ለምኜው ነበር፤ ዛሬም ለመምጣት ከቶ ፈቃድ አልነበረውም፥ ሲመቸው ግን ይመጣል። |
ሄሮድስ የተወለደበትን ቀን ለማክበር ለመንግሥት ባለሥልጣኖች፥ ለጦር ሹማምንትና ለአንዳንድ የታወቁ የገሊላ ነዋሪዎች ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ ይህም ለሄሮዲያዳ ጥሩ አጋጣሚ ሆነላት፤
የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረና ጥሩ የአነጋገር ችሎታ ያለው ሰው ነበረ።
ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በተናገረ ጊዜ ፊልክስ ፈርቶ “አሁን ሂድ፤ ሲመቸኝ ሌላ ጊዜ አስጠራሃለሁ” አለው።
ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን፥ ጴጥሮስም ቢሆን፥ ዓለምም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ አሁን ያለውም ቢሆን፥ በኋላ የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉም የእናንተ ነው።
ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤