1 ቆሮንቶስ 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባብ ተነድፈው እንደ ሞቱ እኛም ጌታን አንፈታተነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑና በእባብ ተነድፈው እንደ ጠፉ፣ እኛም ጌታን አንፈታተን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባቦች እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን እንደ ተፈታተኑት፥ ነዘር እባብም እንደ አጠፋቸው እግዚአብሔርን አንፈታተን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን። |
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።