ሶፎንያስ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ሁሉም የጌታን ሥም እንዲጠሩና በአንድ ትከሻ እንዲያገለግሉት፥ ለሕዝቦች ንጹሕን አንደበት እመልስላቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩ፣ ተስማምተው እንዲያገለግሉት፣ አንደበታቸውን አጠራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያን ጊዜ ሕዝቦች ንጹሕ ንግግር እንዲናገሩ አደርጋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ሁሉም የእኔን የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩና በአንድነት እንዲያገለግሉኝ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ። |
በዚያ ቀን በግብጽ ምድር በከንዓን ቋንቋ የሚናገሩ፥ በሠራዊት ጌታም የሚምሉ አምስት ከተሞች ይሆናሉ፤ ከነዚህም አንዷ የጥፋት ከተማ ተብላ ትጠራለች።
አቤቱ! ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል፤
ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”