ሶፎንያስ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንግሥታትን አጥፍቻለሁ፥ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፥ መንገዶቻቸውን ማንም የማይተላለፍባቸው ባዶ ሆነዋል፥ ከተሞቻቸውም አንድም ሰው እንዳይገኝባቸው፥ ማንም የማይኖርባቸው ሆነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጋቸው ተደምስሷል፤ ማንም እንዳያልፍባቸው፣ መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል፤ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብ “መንግሥታትን አጠፋሁ፤ ምሽጎቻቸውን አፈራረስኩ፤ መንገዶቻቸውን ማንም የማይተላለፍባቸው ባዶ አድርጌአቸዋለሁ፤ ከተሞቻቸውን ሕዝብ የሌለባቸው፥ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አድርጌአቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብን አጥፍቻለሁ፣ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፣ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብን አጥፍቻለሁ፥ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፥ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል። |
እኔም፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፤ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፤ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፤ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤
ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? እንዲያውጅስ የጌታ አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለምን ተቃጠለች?
እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ፥ የከሪታውያን ሕዝብ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የጌታ ቃል በእናንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብሽ እንዳይኖር አድርጌ አጠፋሻለሁ።
በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኳቸው። ስለዚህ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚዘዋወርባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፤ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።
እነሆ፥ እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ በፀሐይ መግቢያ እስካለው እስከ ታልቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ የቀሩትን እነዚህን አሕዛብ በዕጣ ሰጠኋችሁ።