አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።
ዘካርያስ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ “ደስ ብሎአችሁ እንደሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፥ ያለዚያ ግን ተውት” አልኩት። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “የሚበጅ መስሎ ከታያችሁ ዋጋዬን ክፈሉኝ፤ አይሆንም ካላችሁም ተዉት” አልኋቸው፤ ስለዚህ ሠላሳ ብር ከፈሉኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “ብትፈቅዱ ደመወዜን ስጡኝ፤ ባትፈቅዱ ተዉት” አልኳቸው፤ እነርሱም የአገልግሎቴን ዋጋ ሠላሳ ብር ሰጡኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፣ ያለዚያ ግን ተውት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፥ ያለዚያ ግን ተውት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። |
አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቆርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቆራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።