ዘካርያስ 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም እንዲህም ስትል ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ እንደገና በብልጽግና ይሞላሉ፤ ጌታም እንደገና ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ምርጫው ያደርጋታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቀጥለህም እንዲህ እያልህ ስበክ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከተሞቼ እንደ ገና ብልጽግና ይትረፈረፍባቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ገና ጽዮንን ያጽናናል፤ ኢየሩሳሌምንም ይመርጣል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም እንደገና “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከተሞቹ ተመልሰው እንደሚበለጽጉና ኢየሩሳሌምንም እንደ ጥንቱ እንደሚረዳ የራሱ ከተማም እንደሚያደርጋት ተናገር” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ፣ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል። |
በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ።
ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።
የባርያዬን ቃል አጸናለሁ፤ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፥ የይሁዳንም ከተሞች፦ ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ።
ጌታም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርሷም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ ጌታ ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።
በዚያን ጊዜም ድንግሊቱ በሽብሸባ ትደሰታለች፥ ጉልማሶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እለውጣለሁ፥ አጽናናቸዋለሁም፥ ከኀዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ።
በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ።
የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።
የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ዳግም ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ የአትክልት ስፍራዎችንም ያበጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።
ይህም የእስራኤል ልጆች የጦር ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፥ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ።
ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፥ ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።
እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልኩት። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሯቸው፥ የይሁዳንም አገር ለመበተን ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊቆርጡ መጥተዋል” ብሎ ተናገረ።
ጌታም ሰይጣንን፦ “ሰይጣን ሆይ፥ ጌታ ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ጌታ ይገሥጽህ! በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” አለው።