ኢሳይያስ 54:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በጥቂት ቁጣ ለቅጽበተ ዐይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘለዓለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ ጌታ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለ ተቈጣሁ፣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ ነገር ግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣ እራራልሻለሁ” ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እጅግ ከመቈጣቴ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ትቼሽ ነበር፤ ነገር ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሬ እራራልሻለሁ፤ ይላል አዳኝሽ እግዚአብሔር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በጥቂት ቍጣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ በዘለዓለም ቸርነት ይቅር እልሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በጥቂት ቍጣ ለቅጽበተ ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር። Ver Capítulo |