እነርሱንም ለማጥገብ፥ ድርጭቶች ከባሕር ውስጥ ወጡ።
ከመብረቆች ያልራቀች ቀድሞ በተአምር በተደረገው የመቅሠፍት ኀይል የምትመሰል መቅሠፍት በኃጥኣን ላይ መጣች፥ እነርሱ እንደ ክፋታቸው ሚዛን በእውነት ተፈርዶባቸዋልና።