በአንድ ዓይነት ሞት በመመታታቸው ለቍጥር የሚታክቱ ሬሳዎች ነበሯቸው። ቀሪዎቹም ሊቀብሯቸው አልቻሉም፤ የፍሬዎቻቸው አበባዎች ባንድ ጊዜ ረግፈውባቸዋልና።
ሁሉም በአንድነት በአንድ አምሳል ሞቱ፤ ቍጥር የሌላቸው የሞቱ ሰዎች በድኖችም ነበሩ። በአንዲት ሰዓት የከበረች ፍጥረታቸው ፈጽማ ስለ ጠፋች ሕያዋን የሞቱትን ሰዎች ይቀብሯቸው ዘንድ አልቻሉምና።