Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ጥበብ 18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ላንተ ቅዱሳን ግን በጣም ታላቅ ብርሃን ነበር፤ የሚሰሟቸው ነገር ግን የማያያቸው ግብጻውያን እነርሱ ሥቃይ ያልደረሰባቸው በመሆኑ ዕድለኞች ይሏቸዋል።

2 በፊት ለደረሰባቸው በደል፥ የበቀል ጉዳት ባለማድረሳቸው አመሰገኗቸው። ስላለፈው ጥላቻቸውም ይቅርታ ለመኗቸው።

3 ከጨማው በተቃራኒ ለሕዝቦችህ የእሳት አምድን፥ ባልታወቀው ጉዟቸው፥ በተስፋ ስደታቸው፥ ይረዳቸው ዘንድ ለዘብ ያለ ፀሐይን ሰጠሃቸው።

4 እነኛ የማይደበዝዘውን የሕግህን ብርሃን ለዓለም ይሰጡ ዘንድ የላክኻቸውን ልጆችህን፥ በምርኮኝነት ይዘው የነበሩት ግን፥ ብርሃንን አጥተው በጨለማ መታሰር ይገባቸዋል።


ስድስተኛው ተቃርኖ፦ የሞት ምሽትና የድኀንነት ምሽት

5 የቅዱሳኑ ልጆች የሆኑትን ሕፃናት ለመግደል እነርሱ እንደወሰኑ፥ ለአደጋ ከተጋለጡትም መሀል አንድ ልጅ ብቻ እንደተረፈው ሁሉ፥ አንተም ልጆቻቸውን በሙሉ ውሃው፥ ማዕበሉም እንዲያጠፋቸው አደረግህ።

6 አባቶቻችን ያችን ምሽት አስቀድመው ያውቋት ነበር፤ እምነታቸውን በማን ላይ እንደጣሉ ያውቁም ስለ ነበር፥ ቃል ኪዳኑ እንደሚፈጸም እርግጠኞች ነበሩ።

7 ስለዚህም ሕዝቦችህ የጻድቃኑን ደኀንነትና የጠላትን መጥፋት ይጠባበቁ ነበር።

8 በተቀናቃኞቻችን ላይ ባወረድከው በቀል፥ እኛን አከበርከን፥ ወዳንተም ጠራኸን።

9 ከደጋጐች የተፈጠሩ ቅዱሳን ልጆች፥ በምሥጢረ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በስምምነት ይህን ቅዱስ ሕግ አጸደቁ፤ ቅዱሳን በጎውንና ክፉውን ይጋሩ ዘንድ ወሰኑ፤ ያኔውኑም ያባቶችን መዝሙር ዘመሩ።

10 የጠላቶቻቸው ጩኸት ከያለበት አስተጋባ፤ ስለልጆቻቸው የሚያዝኑ ሰዎች ዋይታም ከሩቅ ይሰማል፤

11 ጌታና አገልጋይ ተመሳሳይ ቅጣት ወረደባቸው፤ ተራው ሰውና ንጉሡም የአንድ መከራ ገፈት ጨለጡ።

12 በአንድ ዓይነት ሞት በመመታታቸው ለቍጥር የሚታክቱ ሬሳዎች ነበሯቸው። ቀሪዎቹም ሊቀብሯቸው አልቻሉም፤ የፍሬዎቻቸው አበባዎች ባንድ ጊዜ ረግፈውባቸዋልና።

13 በአስማቶቻቸው ተማምነው ያላመኑት ሁሉ፥ የበኩር ልጆቻቸው በሞቱባቸው ጊዜ፥ ይህ ሕዝብ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምነው ተቀበሉ።

14 ሰላማዊ ጸጥታ በሁሉም ላይ በሰፈነ ጊዜ፥ ሌት ከተጋመሰች በኋላ፥

15 ኃያሉ ቃልህ ከንጉሣዊው ዙፋን እንዳትጠፋ በተፈረደባት መሬት እምብርት ላይ እንደ ጨካኝ ጦረኛ ከሰማይ ዘሎ ወረደ። የማያወላውለውን ትእዛዝህን እንደ ሰላ ሠይፍ ይዞ በመውረድ፥

16 ዓለምን በሞት አጥለቀለቃት፤ ያረፈው በምድር ላይ ቢሆንም ሰማይን ነክቷል።

17 ወዲያው ሕልሞችና አስፈሪ ቅዠቶች አሸበሯቸው፤ ያልጠበቁትም ፍርሃት አስጨነቃቸው።

18 ወዲያና ወዲህ ግማሽ በድን አካላቸው ተጥሏል፤ ስለምንም አንደሚሞቱ ይናገሩ ነበር።

19 ያስጨነቋቸው ሕልሞች ይህ ቅጣት ስለምን እንደ ተፈረደባቸው ሳያውቁት እንዳያልፉ አድርጓቸዋልና።


በበረሃ ውስጥ አንዣቦ የነበረው የዕልቂት አደጋ

20 ይሁን እንዱ የሞት ጽዋ በጻድቃኖችም ላይ ደርሷል። ብዙዎችም በበረሃ አልቀዋል፤ ቁጣው ግን አልበረታባቸውም፤

21 አንድ ንጽሕ ሰው ከመዓቱ አድኗቸዋልና። የተቀደሱ መሣሪያዎቹን፥ ጸሎቱንና የስርየት ዕጣን በመያዝ ቁጣውን ተጋፈጠው፤ አገልጋይህ መሆኑንም በማስመስከር መዓቱን አስወገደ።

22 ጥላቻን አስወገደ፤ በጉልበት አልነበረም፥ በመሣሪያም አልነበረም፥ ለአባቶች ያደረገውን መሐላ፥ የገባውንም ቃል ኪዳን በማስታወስ ቀጪውን ስለ ተስፋው ቃል በመለመን ነበር እንጂ።

23 ቁጣን ባቆመውና ወደ ሕያዋንም እንዳይጠጋ ባገደው ጊዜ፥ አስክሬኖች ተከምረው ነበር።

24 መላው ዓለም በቀሚሱ ላይ ተስሎ ነበር፤ የከበሩ የአባቶች ስሞች በአራቱ ረድፍ ደንጊያዎች፥ ያንተ ግርማም በአክሊሉ ላይ ተቀርጿል።

25 ደምሳሹም ከእነኚህ ራቀ፤ ፈራቸውም፤ ይሄው ቁጣም በቂ ነበር።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos