ገበሬም ይሁን እረኛ፥ በበረሃም የሚሠራ ቢሆን፥ በድንገት እየተያዘ የወደቀበትን የማይታለፍ ዕጣ በግደ ይቀበላል፤ ሁሉም ባንድ የጨለማ ሠንሠለት ታሥረው ነበርና።
ማኅበራቸው በአንዲት የጨለማ እግር ብረት ታስሯልና ያገኛቸው ምትሀት እንዲህ ነው፥ የሚያፏጭ ምትሀት፥ ወይም ጭፍቅ ካሉና ከሚያስጠልሉ ከዛፎች የተነሣ ድምፁ ያማረ የቅርንጫፎች ቃል ወይም ዜማቸው ያማረ የወፎች ድምፅ፥