Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ጥበብ 17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)በግብፃውያን ላይ ፍርሀት በሌሊት እንደ ወደቀችባቸው 1 ፍርድህ ታላቅ ነው፥ ለመናገርም ድንቅ ነው። ስለዚህም የፈጣሪ ትምህርት የሌላቸው ሰውነቶች ሳቱ። 2 ኃጥኣን ቅዱስ ሕዝብን በያዙ ጊዜ፥ በተበረታቱባቸውም ጊዜ፥ ኀያላንም በረዥም የሌሊት ጨለማ በታሰሩ ጊዜ ያንጊዜ በቤታቸው ጣራ ስር ተጋዙ። ከዘለዓለማዊው አገልግሎት ሥርዐትም ሸሸተው ተገኙ። 3 የበደሉትንም ዐስበው በውስጡ ብርሃን በሌለበት ቤት ውስጥ ከዝንጋዔ መጋረጃ በታች ተሰወሩ፥ እጅግም እየተደነቁ በድንጋጤ ቀለጡ፥ በምትሀትም ታወኩ። 4 የያዛቸው አመንዝራ ከድንጋጤ ይጠብቃቸው ዘንድ አልቻለም፥ ነገሩ ስቅጥጥ የሚያደርግ የታላቅ ቃል ድምፅም ያውካቸው ጀመር። የክፉ ምትሀት መልክም ፊቱ ያዘነውን ሁሉ አጠፋ። 5 የእሳቱም ብርሃን አንዲት ሰዓት እንኳ ያበራ ዘንድ አልቻለም፥ የብሩሃን ከዋክብት ብርሃንም ለዚያች ለምታስፈራዋ ሌሊት ጨለማ ያበራ ዘንድ አልቻለም። 6 ነገር ግን ከዚህ ከሚታየው መልክ ይልቅ ግርማው ፍጹም የሆነ፥ ከማይታዩትም መልኮች ይልቅ የከፋ ብቸኛ እሳት ድንገት ታያቸው። 7 በሚሳደቡት ላይ የትዕቢት ዘለፋ ሊሆንባቸው የስንፍና ድካም የሆነ የሟርት ሥራን ከወርቅና ከብር አደረጉ። 8 ከታመመች ሰውነት ሁከትንና ድንጋጤን ያስወግዱ ዘንድ ተስፋ የሰጡ እነዚህን ፍርሀት አሳመማቸው፥ ለሣቅም የተገቡ ሆኑ። 9 የሚያውከው ነገር ምንም ባያስፈራቸው የሚበርር ተሓዋሲ እንቅስቃሴና የእባቦች ጩኸት አባረራቸው። አስደንግጦም አሸሻቸው። ከሁሉ አቅጣጫ የሚሸሽ ነፋስንም ማየት አልተቻላቸውም። 10 የክፉ ሰው ሥራው የሚያስመሰክርበትና የሚያስፈርድበት ዐመፅ ነው፥ ሁልጊዜም እየታወቀውና ዕውቀት ባለው ሕሊና እየተመለከተ ክፉና ጠማማ ሥራን ይቀበላል፥ ይሠራልም። 11 ፍርሀት ምንም አይደለም፥ ነገር ግን የፍርድ ጥርጥርን በሕሊና ያሳድራል። 12 ጥቂት ወይም ጐደሎ የልቡና ጥርጥር ብትኖርም ባለማወቅ ነው፥ በስንፍናም ነው፥ ለፍርድም መንገድ የምትሰጥ ናት ተብላ ትታሰባለች። 13 በእውነት ሊታገሡአት ከማይቻል ከሲኦል ጕድጓድ የወጣች ያች ሊታገሡአት የማይቻል ሌሊት እነርሱን በሸፈነቻቸው ጊዜ ያችን ቀን ተኝተው ነበር። 14 የሚያስደነግጡ አጋንንት አስደንግጠዋቸዋልና፥ ምትሀትን በማሳየት የሚያሳድዱአቸው አሉ፥ የሰውነትንም ተስፋ የሚያደክም አለ፥ ያልጠበቁትና ያልተጠራጠሩት ፍርሀትና ድንጋጤም ድንገት ደረሰባቸው። 15 በዚያም ያለው ማንኛውም ሁሉ እንዲህ ነው፥ የወደቀም ቢሆን፥ በእግር ብረት ወይም ያለ እግር ብረት ታስሮ በእስር ቤት የሚጠበቅም ቢሆን፥ 16 አራሽም ቢሆን፥ እረኛም ቢሆን፥ በምድረ በዳ ተቀምጦ ምድርን በማረስ የሚደክም ምንደኛም ቢሆን፦ ያገኘችውን ያችን አስጨናቂ መከራ ታግሦአልና። 17 ማኅበራቸው በአንዲት የጨለማ እግር ብረት ታስሯልና ያገኛቸው ምትሀት እንዲህ ነው፥ የሚያፏጭ ምትሀት፥ ወይም ጭፍቅ ካሉና ከሚያስጠልሉ ከዛፎች የተነሣ ድምፁ ያማረ የቅርንጫፎች ቃል ወይም ዜማቸው ያማረ የወፎች ድምፅ፥ 18 ወይም በኀይል የሚሄድ የውኃ ሿሿቴ ድምፅ፥ ወይም በማስፈራራት የሚገለባበጡ የዋሻዎች ድምፅ፥ ወይም የሚሮጡና ሩጫቸው የማይታይ የእንስሳት ሩጫ፥ ወይም በሚያስፈራ ቃል የሚጮኹ የአውሬዎች ጩኸት፥ ወይም ከአዕዋፍና ከአራዊት ድምፅ የተነሣ እርስ በርሳቸው ድምፅን ለዋውጠው የሚመልሱ የሚያስፈሩ የተራራዎች ድምፅ ነው። አስደንግጦም ያጠፋቸው መከራ እንዲህ ነው። 19 ዓለሙ ሁሉ በሚያበራ ብርሃን ይበራ ነበርና፥ ያለማቋረጥና ያለመከልከልም ሥራውን ይፈጽም ነበርና። 20 እነዚህን ግን ብቻቸውን ይወስዳቸው ዘንድ ያለው የጨለማ ምሳሌ የሆነው የሌሊት ክብደት ሰወራቸው፥ እነርሱ ራሳቸውም ለራሳቸው ከጨለማ የጸኑ ናቸው። |