ለሕዝብህ ያደረግኸው ግን እንደምን የተለየ ነው የመላእክትን ምግብ ሰጠኻቸው፤ ሁሉንም የሚያስደስት፥ ጣዕሙም ለሁሉም የሚስማማውን የሰማይ መና ያለመሰልቸት አቀረብክላቸው።
ስለ ፍሬውም ፋንታ የመላእክትን ምግብ ለሕዝብህ መገብኻቸው፥ ያለ ድካም የተዘጋጀ፥ ጣዕሙም ከሚጣፍጠው ሁሉ የሚበልጥ፥ ጣዕምንም ሁሉ የሚያስንቅ ኅብስትን ከሰማይ ላክህላቸው።