ቲቶ 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽማግሌዎች በመጠን የሚኖሩ፥ ክብራቸውን የሚጠብቁ፥ ራሳቸውን የሚቈጣጠሩ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም በእውነት የጸኑ እንዲሆኑ ምከራቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አረጋውያን ጭምቶች፣ የተከበሩ፣ ራሳቸውን የሚገዙና በእምነት፣ በፍቅርና በትዕግሥት ጤናማነት ያላቸው እንዲሆኑ ምከራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዕድሜ የገፉ ወንዶች፥ በመጠን የሚኖሩ፥ ክብራቸውን የሚጠብቁ፥ ጠንቃቆች፥ በእምነትና በፍቅር በትዕግሥትም ጤናማዎች እንዲሆኑ ምከራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤ |
ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ የመቶ ዓመት ሳይሆነው የሚሞት እንደተረገመ ኃጢአተኛ ይታያል።
ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ፥ የአጋንንት ሠራዊት አድረውበት የነበረው ሰው፥ ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ ፍርሃትም አደረባቸው።
ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ፥ ልቡም ተመልሶ፥ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።
እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኩነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ “አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ፤” ብሎ መለሰለት።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤
ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለሐሰተኞችም፥ በውሸትም ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው።
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥