ሮሜ 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሊቱ አልፎአል፤ ቀኑም ቀርቧል፤ እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን የጦር መሣሪያ እንልበስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሊቱ ሊያልፍ፣ ቀኑም ሊጀምር ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን፣ የብርሃንን ጦር ዕቃ እንልበስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱ እያለፈ ነው፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ ስለዚህ በጨለማ የሚሠራውን ሥራ እንተው፤ የብርሃንን የጦር መሣሪያ እንልበስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌሊቱ አልፎአል፤ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማን ሥራ ከእና እናርቅ፤ የብርሃንንም ጋሻ ጦር እንልበስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። |
በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።
አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።
አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ልጆች ሆይ፥ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል ሲባል እንደ ሰማችሁት አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፤ በዚህም ይህ የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን።