ራእይ 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፤ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድል የሚነሣም እንደ እነርሱ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ እኔም በአባቴና በመላእክቱ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድል የሚነሣ እንደ እነርሱ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ ስሙን በአባቴና በመላእክቱም ፊት አስታውቅለታለሁ፤ የሕያዋን ስም ከሚመዘገብበት ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስሰውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፤ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፥ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ። |
አንተም ደግሞ በሥራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ! ከእኔ ጎን በመቆም ከቀለሜንጦስ ጋር አብረው በወንጌል ሥራ ተጋድለዋልና እነዚህን ሴቶችና የተቀሩትን በሕይወት መጽሐፍ የተጻፉትን ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩትን እንድትረዱአቸው እለምንሃለሁ።
ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ ከጥልቁም ሊወጣ ነው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች አውሬው አስቀድሞ እንደ ነበረ አሁን ደግሞ እንደሌለ፥ ነገር ግን ተመልሶ እንደሚመጣ ሲያዩ ይደነቃሉ።
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።
ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ድርሻውን ያጎድልበታል።
ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዓምድ አደርገዋለሁ፤ ወደፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለትም ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአዲሲቱን ኢየሩሳሌምን ስም፥ እንዲሁም አዲሱን ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱም መገደል የሚጠብቃቸውን የሌሎች አገልጋዮች የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪሞላ ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተነገራቸው።
እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በየቀኑ እየመጣ እስራኤልን እንደሚገዳደር ታያላችሁ? ይህን ሰው ለሚገድል፥ ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ ሴት ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያደርገዋል” ይባባሉ ነበር።