Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትለብስ ተሰጥቶአታል።” ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሚያንጸባርቅና ንጹሕ፣ ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት።” ከተልባ እግር የተሠራው ቀጭን ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሚያንጸባርቅና ንጹሕ የሆነ ውብ ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት፤ ቀጭኑ ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል።” ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 19:8
21 Referencias Cruzadas  

አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።


ሀብታም እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ የምትጐናጸፈውን ነጭ ልብስ፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳልበትን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።


ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ የሥጋም ሐሳብ ምኞቱን እንዲፈጽም አትፍቀዱለት።


ልብሱም በምድር ላይ ማንም አጣቢ አጥቦ ሊያነጣው በማይችልበት ሁናቴ እጅግ ነጭ ሆነ።


‘ወዳጄ ሆይ! የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ።


ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ጻድቃንህም ደስ ይበላቸው።


ወርቀ ዘቦም አለበስሁሽ፥ ከጥሩ ቆዳ የተሠራ ጫማ አደረግሁልሽ፥ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ፥ ውድ መደረቢያም ደረብሁልሽ።


እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤


እነርሱም በዚህ ሲገረሙ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤


ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


ለራስዋም የአልጋ ልብስ ትሠራለች ጥሩ በፍታና ቀይ ግምጃ ትለብሳለች።


ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛው አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ አንዳች የበግ ጠጉር በላያቸው አይሁን።


ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ንጹሕ የጌጥ ልብስ ለበሱ፤ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ።


በሰማይም ያሉት ሠራዊት ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በነጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።


መስታወቱን፤ ከጥሩ በፍታ የተሠራውን ልብስ፤ የራስ ጌጡን፤ ዐይነ ርግቡን ሁሉ ይነጥቃቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios