ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።
ራእይ 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉን፥ ዙፋኑንና ትልቅ ሥልጣንን ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ ነገር ግን እግሮቹ የድብ፣ አፉ ደግሞ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር፤ ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን እንዲሁም ታላቅ ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያየሁት አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፥ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው። |
ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።
ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የከዳተኝነታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኩላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ነቅቶ ይጠብቃል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ከድንክ አልጋና ከአልጋ የእግር ቁራጭ ጋር ይድናሉ።”
ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።
ታላቁም ዘንዶ ወደ ታች ተጣለ፤ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
በመጀመሪያው አውሬ ስም፥ በሙሉ ሥልጣን ይሠራ ነበር። ወደ ሞት የሚያደርሰው ቁስል ለተፈወሰለትም ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።
ያየሃቸውም ዐሥሩ ቀንዶች ገና ያልነገሡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።