ራእይ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኩንና አባቱን እንድናገለግልም መንግሥትና ካህናት ላደረገን፣ ለርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን! አሜን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንድናገለግል ንጉሦችና ካህናት ላደረገን፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ኀይል ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን። |
እናንተ ግን የጌታ ካህናት ትባላላችሁ፤ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፥ በሀብታቸውም ትከብራላችሁ።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ለእርሱ ክብርና የዘለዓለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።
እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ክብር፥ ግርማ፥ ኃይልና ሥልጣን ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንም እስከ ዘለዓለምም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
እኔ ዮሐንስ፥ ከእናንተ ጋር አብሬ በኢየሱስ መከራውንና መንግሥቱንና ጽናቱን የምካፈል ወንድማችሁ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
የመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆነ ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ለሺህ ዓመት ይነግሣሉ።